Fana: At a Speed of Life!

ህዝበ ሙስሊሙ በዓል ሲያከብር በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን ይገባል-አቶ ርስቱ ይርዳው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው 1 ሺሕ 496ኛውን የመውሊድ በአልን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው፥ ነብዩ መሐመድ በእስልምና ሀይማኖት በነበራቸው አስተምህሮት የሰው ልጆች ያለ ዘርና ሃይማኖት ልዩነት የምድር ፍጡራን ሁሉ እኩል መሆናቸውን ሲያስተምሩ እንደነበር ተናግረዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ በአሉን ሲያከብር እንደ ከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት በመደጋገፍና በመተሳሰብ በአሉን ማክበር እንዳለበትም ገልጸዋል።
በተለይ በሀገራችን በተከፈተው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን ይገባልም ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት የሀገርን ህልውና ለማስጠበቅ በርካታ ሙስሊም ወንድሞቻችን በጦር ግንባር ላይ ሆነው ከሌሎች የሀይማኖት ተከታይ ወገኖቻቸው ጋር ሆነው የህይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ዛሬ በፈተና ላይ ሆነን የምናከብረው በአል ነገ በታላቅ ደስታና ተድላ ላይ ሆነን እንደምናከብር ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል።
ዘንድሮ የተከበሩ ህዝባዊም ሆነ ሀይማኖታዊ በአላት በውስብስብ ሀገራዊ ችግሮች ውስጥ ሆነን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ያጋጠመንን ችግር በመወጣት የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ እውን እናደርጋለን ሲሉ በመግለጫቸው አመልክተዋል።
በህዝብ ይሁንታና ፍላጎት የተመሰረተው መንግስት ወደ ስራ በገባበት ማግስት የሚከበረው የመውሊድ በአል በአዲስ አስተሳሰብ እና በአዲስ መንፈስ ህዝባችንን ለማገልገል በላቀ ቁርጠኝነት የምንሰራበት ጊዜ ላይ እንገኛለንም ብለዋ።
አሸባሪው ትህነግ በከፈተብን ወረራ በርካታ ዜጎቻችን ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀል በማይመች ሁኔታ ላይ ሆነው በአልን ለማክበር የተገደዱበት ወቅት ላይ መሆናቸውን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ከፊት ለፊታችን የተደቀነብንን ፈተና በጽናት በማለፍ ነገ አዲስ የተስፋ ብርሀን እናያለን ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለመላው ህዝበ ሙስሊም እንኳን ለ1 ሺሕ 496ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person and sitting
5,876
People Reached
840
Engagements

-2.3x Lower

Distribution Score
Boost Post
348
28 Comments
10 Shares
Like

Comment
Share
May be an image of 1 person and sitting
0
People Reached
5
Engagements
Distribution Score
Boost Post
5
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.