Fana: At a Speed of Life!

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር በተለመደ ጨዋነት ዕለቱን ማሰለፍ ይኖርበታል ተባለ

አዲስአበባ፣ ግንቦት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር በተለመደ ጨዋነት መሆን ይኖርበታል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ትናንት የተደረገውን የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሃግብር በሰላም መከበር እና በነገው ዕለት ለሚከበረው ለ1 ሺህ 442ኛው አመተ ሂጅራ የኢድ አልፈጥር በዓል አከባባር ዙሪያ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጂ ሱልጣን አማን ኤባ እንዳስታወቁት፥ በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ የተደረገው የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሃግብር አንድነታችን ያጠናከረ፣ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ኢትዮጵያዊ እሴታችንን በግልጽ የታየበት ነው ብለዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ 1 ሺህ 442ኛውን አመተ ሂጅራ የኢድ አልፈጥር በዓል ሲያክብርም የሃገርን አንድነት በመጠበቅ፣ የተቸገሩ ወገኖችን ከመርዳት ባለፈ ለኮቪድ19 ወረርሽኝ በማያጋልጥ መንገድ ሊሆን እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ባዩ ሽጉጤ በበኩላቸው፥ ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር በትናንትናው ዕለት በኢፍጣር ፕሮግራም ላይ ያሳየውን ጨዋነት እና አንድነት በመድገም ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስቴዲየም ለሚደረገው የአከባበር ስነስርዓት ካለምንም የጸጥታ ችግር ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ሃላፊው መግለጻቸውን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.