Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡ የገና በዓልን ሲያከብር በጸጥታ ችግር ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ሊያስብ ይገባል- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ነገ የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል መልካም በዓል እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል።

በክልሉ ባለፉት ወራት በመተከል ዞን በጸጥታ ችግር የንጹሃን ዜጎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን፣ በንብረትና በዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ሠብአዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

በመሆኑም የእምነቱ ተከታዮች የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ሲያከብሩ፣ እነዚህን የተቸገሩ ወገኖች በማሰብና የታቻላቸውንም በመደገፍ እንዲያከብሩ የክልሉ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን በማክበር ሂደት በሚያደርጉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የህብረተሰቡ የጤና ስጋት የሆነውን የኮቪድ-19 መከላከያና የጥንቃቄ መንገዶችን በልዩ ትኩረት በመተግበር ራቸውን ከቫይረሱን ሊጠብቁ እንደሚገባም የክልሉ መንግስት ጥሪ ማቅረቡን ከክልሉ የኮመዪኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ነገ የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የበረከት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.