Fana: At a Speed of Life!

ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ይገባል – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ ይገባል ሲል ምክረ ሃሳብ አስቀምጧል።

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በተለይም ቫይረሱ የሌለባቸው ሰዎች ጭምብልን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያሳይ አሳማኝ ምክንያት የለም ማለቱ የሚታወስ ነው።

አሁን ላይ ባወጣው መግለጫ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ እንደሚረዳ አንስቷል።

ከዚህ አንጻርም ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎች ጭምብል አድርጎ መንቀሳቀስ ቫይረሱ እንዳይተላለፍና እንዳይሰራጭ ይረዳል ብሏል።

በፋብሪካዎች የተመረቱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በተለይም ሰው በሚበዛባቸውና ቫይረሱ ሊተላለፍባቸው በሚችልባቸው ቦታዎች ላይ ማድረግ እንደሚገባም ምክረ ሃሳብ አስቀምጧል።

ከዚህ አንጻርም መንግስታት ዜጎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን እንዲያበረታቱ እንመክራለንም ብሏል ድርጅቱ በመግለጫው።

ይሁን እንጅ ጭምብል የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የሚያግዝ እንጅ ብቻውን ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዳ እንዳልሆነ መገንዘብ ይገባልም ነው ያለው።

በርካታ ሃገራት ሰዎች ከቤታቸው ሲወጡ ጭምብል ማድረግን እንደ ግዴታ አስቀምጠዋል።

የዘርፉ ባለሙያዎችም ጭምብል ማድረግ እንዲሁም አዘውትሮ እጅ መታጠብና የሚሰጡ ምክሮችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ይመክራሉ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.