Fana: At a Speed of Life!

ሆንግ ኮንግ ለነዋሪዎቿ የገንዘብ ስጦታ ልታበረክት ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሆንግ ኮንግ ለነዋሪዎቿ የ1 ሺህ 200 ዶላር ገንዘብ ልትሰጥ ነው።

ስጦታው የነዋሪዎችን የገንዘብ አቅም ለማጎልበት እና ያለባቸውን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማቃለል ያለመ ነው ተብሏል።

በዚህም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ 7 ሚሊየን ቋሚ ነዋሪዎች የዚህ ስጦታ ተጠቃሚዎች ናቸው።

ከዚህ ባለፈም የሆንግ ኮንግ ባለስልጣናት የቤት ኪራይን እና የገቢ ግብርን ለመቀነስ መወሰናቸውን ገልጸዋል።

የአሁኑ ማበረታቻ በሆንግ ኮንግ ለወራት ተካሂዶ በነበረው ህዝባዊ አመጽ ምክንያት የደረሰውን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

ይህን ተከትሎም የሆንግ ኮንግ አስተዳደር በተቃውሞና በቅርቡ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የተጎዳውን ኢኮኖሚ ለመደጎም የሚያስችል ፕሮጀክት ቀርጿል።

የአሁኑ ስጦታም የዚህ አካል መሆኑም ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.