Fana: At a Speed of Life!

ሆንግ ኮንግ ምርጫዋን አራዘመች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሆንግ ኮንግ በመጪው መስከረም ልታካሂደው የነበረውን የፓርላማ ምርጫ አራዘመች፡፡

ሆንግ ኮንግ በኮሮናቫይረስ መስፋፋት ምክንያት በመጪው መስከረም ሊካሂድ የታቀደውን የፓርላማ ምርጫ ማራዘሟ ታውቋል፡፡

ምርጫውም ለአንድ ዓመት መራዘሙ ነው የተነገረው፡፡

የምርጫውን መራዘም ተከትሎም ተቃዋሚ ፓርቲ መንግሥት ወረርሽኙን እንደ ምክንያት በመጠቀም ሕዝቡ የሚፈልገውን እንዳይመርጥ እያደረገ ሲሉም ከሰዋል ነው የተባለው፡፡

የሆንግ ኮንግ ዋና አስተዳዳሪ ካሪ ላም የምርጫውን ጊዜ ለማራዘም የአስቸኳይ ጊዜ የማወጅ ሥልጣናቸውን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አስታውቀው÷ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ከሰጠሁት ውሳኔዎች ሁሉ ይህ እጅጉን አስቸጋሪ ውሳኔ ነው ብለዋል።

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ ሲሆን በ24 ሰዓት ውስጥም 121 ሰዎች በቫረሱ ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላም በግዛቷ 3ሺህ273 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 27 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.