Fana: At a Speed of Life!

ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ቤተሰቦች እንዲሁም በዚህ ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመደገፍ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጉባኤ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አዘጋጅነት ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና ቤተሰቦች፤ በዚህ ሂደት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለመደገፍ ታላቅ የድጋፍ ማሰባሰቢያ የዙም ጉባኤ ተካሄደ።

ትናንት በተካሄደው ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እንደገለጹት ዳያስፖራው በገንዘብ፣ በቁሳቁስና በእውቀት እያደረገ ላለው ተግባራዊ አጋርነትና ድጋፍ አመስግነዋል።

መንግስት በሃገር ውስጥም በውጭም ያሉ ወገኖችን አስተባብሮ በመላው ሀገሪቱ ሰላም፣ አንድነትና ብልጽግና እንዲረጋገጥ ማንም ኢትዮጵያዊ ባይተዋር የማይሆንባት ሀገርን የመገንባቱ ግስጋሴ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው በዚህ ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ከመከላከያ ጎን እና አብረው እየተዋደቁ ላሉ ጀግኖች ድጋፍ በማድረግ ላይ ላሉ የዳያስፖራ ወገኖች ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

ዳያስፖራው ወገናችን የጽንፈኛው የህወሓት ቡድን ቅጥረኞች የሚነዙትን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የማክሸፍ ስራዎችን በበለጠ ቅንጅት እንዲሰራም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ እንዳሉት ደግሞ መንግስት ህግን የማስከበር ዘመቻ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዳያስፖራው በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያሳዩት አጋርነት ድጋፍ ለተመዘገበው ድል አስተዋጽኦ እንደነበረው ገልጸዋል።

ይህ ድጋፍ በቀጣይ ለሚኖረው ሃገራዊ ግዳጅም የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።

በአሜሪካ የኢፌዴሪ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያ የተግባር ምክር ቤት ምንም እንኳ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም እጅግ ውጤታማ የወገን ደራሽ ተግባራዊ ስራዎችን እያከናወነ ነው።

ኤምባሲውም ከምክር ቤቱ ጋር መስራቱን እንድሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

የተግባር ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ደምለው አልማው በዚህ ውጤታማ የድጋፍ ማሰባሰብ ለተገኙ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና ሌሎች ተሳታፊዎች ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ምክር ቤቱ በቀጣይም ኢትዮጵያና ኢትዮጵውያንን የሚጠቅሙ ሰፊ ተግባራትን መስራቱን ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

በዛሬው ድጋፍ የማሰባሰብ ፕሮግራም ከ21 ሺህ ዶላር በላይ የተገኘ ሲሆን ምክር ቤቱ በከፈተው የጎፈንድ ሚ አካውንት እስካሁን ከ330 ሺህ ዶላር በላይ ተሰባስቧል።

በዝግጅቱ ላይ በርካታ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የጦር መኮንኖች፣ አምባሳደሮች፣ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞችና በርካታ ታዋቂ ሰዎች ከአሜሪካ፣ ካናዳ እና አውሮፓ መሳተፋቸውን በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመረዳት ችለናል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.