Fana: At a Speed of Life!

ለህዝብ አንድነት፣ መተሳሰብና ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ችግሮችን መፍታት ይገባል- ሲኖዶሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለህዝብ አንድነትና መተሳሰብ፣ ለዜጎች ሁለንተናዊ ደህንነት እና የህይወት ዋስትና ቅድሚያ በመስጠት ችግሮችን በሰላማዊ እና በሰለጠነ መንገድ ሊፈቱ ይገባል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አሳሰበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ  ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ላይም መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ቅድሚያ በመስጠት  ሊሰራ እንደሚገባ ነው ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳሰበው።

መጪው ሀገራዊ ምርጫም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ  ሁሉም የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ሊወጣ ይገባል ብሏል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብም ወደ መጨረሻ ምዕራፍ እየተቃረበ በመሆኑ ህዝቡ ድጋፉን አጠናቅሮ ሊቀጥል እንዲገባ በመግለጫው ላይ አመልክቷል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተም ሁሉም ዜጎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ያሳሰበው ሲኖዶሱ  የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎትም ይህን ባገናዘበ መንገድ ሊቀጥል ይገባል ብሏል።

በለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.