Fana: At a Speed of Life!

ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊየን ብር ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው ዓመት ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 605 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ከዚህ ውስጥ በሚያዚያ ወር ብቻ 79 ሚሊየን ብር መሰብሰቡም ታውቋል።

ገንዘቡ የተሰበሰበው በ8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብርና በቦንድ ሽያጭ ሣምንት መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሃም ገልጸዋል።

ለግድቡ ግንባታ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ነበር።
ይሁንና በወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረግ ባለመቻሉ ለገቢ ማሰባሰቡ እንቅፋት በመሆኑ 605 ሚሊየን ብር ተሰብስቧል።

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ እስካሁን 13 ነጥብ 54 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ጽሕፈት ቤቱ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።
#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.