Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሰራዊቱ 8 ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፕሪሚየርሊግ ሼር ካምፓኒ ለመከላከያ ሰራዊቱ 8 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡

ሼር ካምፓኒው በስሩ የሚገኙትን 18 የእግር ኳስ ቡድኖች በማስተባበር ነው ገንዘቡን የሰበሰበው፡፡

የርክክብ ስነስርአቱ በመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራሮች እና በታዋቂ አርቲስቶች መካከል በተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኤሳያስ ጅራ ጠላቶቻችን ሆነ ብለው ሀገርን የማፍረስ አጀንዳ ይዘው በሚንቀሳቀሱበት በዚህ ሰአት ከመበታተን ይልቅ አንድነት የተሻለ መሆኑን ለማረጋገጥ እግር ኳስ ታላቅ ማሳያ ነው ብለዋል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ብርጋዴር ጄነራል አስፋው ማመጫ ÷ኢትዮጵያን በመታደግ ዘመቻ ላይ አርቲስቶች እና ስፖርተኞች በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ስም እና ዝና በመጠቀም ሀገር ፈተና ላይ በወደቀች ሰአት አለሁ በማለት ታላቅ አሻራ አሳርፈዋል ብለዋል።

የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው ÷የመንግስት አካላትም ሆኑ ለጋሱ የኢትዮጵያ ህዝብ በራሳቸው ተነሳሽነት እያደረጉት የሚገኘት ጠንካራ ውግንና የሰራዊታችንን ተወዳጅነት የሚያሳይ ነው ሲሉ መናገራቸውን ከመከላከያ የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.