Fana: At a Speed of Life!

ለሚ ኩራ የአዲስ አበባ 11ኛ ክፍለ ከተማ በመሆን ፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሚ ኩራ የአዲስ አበባ 11ኛ ክፍለከተማ በመሆን በምክር ቤቱ ጸድቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከሰዓት ውሎው ክፍለ ከተሞችንና ወረዳዎችን እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ወሳኔ አስተላልፏል፡፡

አዲሱ አደረጃጀት የነዋሪዎችን ብዛት በማመጣጠን ፣ አዳጊ የሆነውን የአገልግሎት ተደራሽነትና የማስተዳደር አቅምን በማጎልበት ለከተማው ነዋሪዎች ሚዛናዊ በሆነ ርቀትና ተደራሽ በሆነ መልኩ የአገልግሎት አቅርቦት በማመቻቸት ነዋሪው ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚረዳ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

በመድረኩ ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲሱ ክፍለ ከተማ ተጨማሪ ይዞታ ሳይሆን ከዚህ ቀደም ከነበረው ከቦሌ እና ከየካ ክፍለከተሞች በመክፈል የተዋቀረ ነው ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያደረገ ሲሆን ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን ዳግም የማቋቋሚያ አዋጁንም ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በዚህም ለሚ ኩራ ክፍለከተማ የአዲስ አበባ 11ኛው ክፍለ ከተማ እንዲሆን ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው መወሰኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.