Fana: At a Speed of Life!

ለምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች  ኮቪድ 19 የተመለከተ  ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 (ኤፍ. ቢ. ሲ) ለምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች የኮቪድ 19  የተመለከተ ስልጠና በመሰጠት ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ለአንድ ቀን የሚሰጠው ይህ ስልጠና የኮቪድ-19 ምንነት እና ሊወስዱ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ነው ተብሏል።

ከዚያም ባለፈ ስልጠናው ቫይረሱ የመስፋፋት እድሉ ቢጨምርና መስማት የተሳነው ሰው በለይቶ ማቆያ የሚገባበት አጋጣሚ ቢፈጠር የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚዎች ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ስልጠናው የጤና ሚኒስቴር፣የኢትዮጵያ ፕብሊክ ኸልዝ ኢንስቲቲዩት  ከኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሄራዊ ማህበር ጋር በመተባበር  እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.