Fana: At a Speed of Life!

ለሳምሰንግ ጋላክሲ ተጠቃሚዎች የደረሰው ያልታወቀው መልዕክት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም ላይ የሚገኙ የሳምሰንግ ጋላክሲ ስልክ ተጠቃሚዎች በትናንትናው ዕለት በስህተት ለመረዳት አስቸጋሪ ነው የተባለ የ1 ቁጥር መልዕክት ወደ ስልካቸው ገብቷል።

ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በርካታ የጋላክሲ ስልክ ተጠቃሚዎች ዘንድ ብዥታን መፍጠሩ ነው የተነገረው።

ተጠቃሚዎቹ መልዕክቱ ከሳምሰንግ ˝ፋይንድ ማይ ሞባይል˝ መተግበሪያ እንደተላከ ያስታወቁ ሲሆን፥ ይህም ለጋላክሲ ስልክ ተጠቃሚዎች 1 ቁጥርን ሁለት ጊዜ መላኩ ተጠቁሟል።

መልዕክቱን የላከው ˝ፋይንድ ማይ ሞባይል˝ መተግበሪያ፥ ስልኮችን ከርቀት መቆጣጠር እና መዝጋት መቻሉ ደግሞ በተጠቃሚዎች ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል።

ሆኖም ሳምሰንግ ኩባንያ ጉዳዩ ከደህንነት ችግር ጋር እንደማይገናኝ ለተጠቃሚዎቹ ይፋ አድርጓል፤ ክስተቱ የተፈጠረው የውስጥ ሙከራ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት መሆኑን አስረድቷል።

ምንጭ፡- www.gizmodo.co.uk/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.