Fana: At a Speed of Life!

ለሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮስታሪካ አስተናጋጅነት በ2022 ለሚካሄደው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከታንዛኒያ አቻው ጋር ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን ያደረጋቸው ሦስት የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታዎችን በአሸናፊነት ተወጥቷልም ነው የተባለው፡፡
በቀጣይ ከታንዛኒያ አቻው ጋር ለሚያደርገው የአራተኛ የማጣርያ ዙር ጨዋታ ዛሬ ታህሳስ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ሀያት አካባቢ በሚገኘው የካፍ የልዕቀት ማዕከል የብሔራዊ ቡድን የስፖርት ትጥቃቸውን በመያዝ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ጥሪ የተደረገላቸው 28 ጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ከአዲስ አበባ ከተማ፦ አርያት ኦዶንግ ፣ ማክዳ አሊ
2. ከአዳማ ከተማ፦ እየሩሳሌም ሎራቶ ፣ ናርዶስ ጌትነት
3. ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ ብዙአየሁ ታደሰ ፣ ትእግስት ሃይሌ ፣ አረጋሽ ካልሳ
4. ከድሬ ዳዋ ከተማ፡- ብርቄ አማረ ፣ ቤተልሔም ታምሩ ፣ ባንቺይርጋ ተስፋዬ
5. ከባህር ዳር ከተማ፡- ባንቺአየሁ ደመላሽ
6. ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፡- ኝቦኝ የን ፣ መስከረም ኢሳያስ ፣ ገነት ኤርምያስ
7. ከመከላከያ ስፖርት ክለብ፡- መዓድን ሣህሉ ፣ ነፃነት ፀጋዬ ፣ ገነት
ኃይሉ ፣ ቤተልሔም በቀለ ፣ እፀገነት ግርማ ፣ አይናለም አደራ ፣ መሳይ ተመስገን
8. ከሀዋሳ ከተማ፡- ቱሪስት ለማ ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ ፣ ቅድስት ቴቃ
9. ከቅዱስ ጊዮርጊስ፡- ንግስት አስረስ ፣ ሰናይት ሼጎ
10. ከቦሌ ክፍለ ከተማ፡- ንግስት በቀለ ፣ ንጋት ጌታቸው መሆናቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላታክል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 7 people and text
0
People reached
0
Engagements
Distribution score
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.