Fana: At a Speed of Life!

ለሽብር ተግባር ህገ-ወጥ መታወቂያ እያዘጋጀ ሲያድል የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሽብር ተግባር የሚውል ህገ-ወጥ መታወቂያ በማዘጋጀት ሲያድል የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የድሬዳዋ አስተዳደር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ ኮሚቴ አስታወቀ።
 
ግለሰቡ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር መዋሉን የእዙ አባል የሆነው የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የጎሮ ፖሊስ ጣቢያ አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር ያሲን አህመድ ገልጸዋል።
 
ግለሰቡ በከተማው ሣቢያን ቀበሌ ቶኒ እርሻ በተባለ አካባቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ሰነዶችን በማዘጋጀት ላይ እንዳለ እጅ ከፍንጅ መያዙን ተናግረዋል ።
 
ፖሊስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ መሰረት ባደረገው ፍተኛ ከተያዙ በርካታ ቁጥር ያላቸው የድሬዳዋ አስተዳደር እና የኦሮሚያ ክልል ሀሰተኛ መታወቂያ ካርዶች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
 
ከመታወቂያ ካርዶቹም መካከል ዝግጅታቸው የተጠናቀቀ እንዲሁም የግለሰቦች ፎቶና ማህተም ያላረፈባቸው በዝግጅት ሂደት ላይ ያሉ እንደሚገኙበትም ጠቅሰዋል።
 
በተጨማሪም መታወቂያ የሚዘጋጅላቸው የበርካታ ግለሰቦች ፎቶግራፎች፣ ማህተሞችና ሌሎች ህገወጥ ሰነዶች መገኘታቸውን አመልክተው÷ፖሊስ ተጠርጣሪ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
በተመሳሳይ በሣቢያ ጎሮና አካባቢው በተደረገ ቁጥጥርና የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ቦንቦች፣ ሽጉጦችና ሌሎች ተቀጣጣይ መሣሪያዎች መገኘታቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
መሳሪያ የተገኘባቸውን ጨምሮ ከከህወሓትና ከሸኔ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.