Fana: At a Speed of Life!

ለቀጣዩ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር 8 ቢሊየን ችግኞች እየተዘጋጁ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቀጣዩ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር 8 ቢሊየን ችግኞች እየተዘጋጁ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና በምግብ ዋስትና ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ሳኒ ረዲ እንዳሉት በ2013/14 የምርት ዘመን ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተከሉ 6 ቢሊየን፣ ለጎረቤት ሃገራት 1 ቢሊየን እንዲሁም በማጓጓዝ እና በተለያየ ምክንያት የሚበላሹ ችግኞችን ለመተካት ተጨማሪ 1 ቢሊየን በድምሩ 8 ቢሊየን ችግኞች ተዘጋጅተዋል፡፡

ወደ 40 ሺህ የሚጠጉ የችግኝ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን የጠቀሱት ሚኒስትር ዲኤታው፣ የሚተከሉት ችግኞች ለደን ሽፋን፣ ለምግብነት እና ለቀርከሀ ቁሳቁስ ምርት የሚውሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

ቀጣዩን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ለማከናወን ለክልሎች ወደ 60 ሚሊየን ብር በጀት መያዙንም አመላክተዋል፡፡

ባለፉት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሮች የተተከሉ ችግኞች ከ80 በመቶ በላይ እንደጸደቁ መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.