Fana: At a Speed of Life!

ለተፈናቃዮች የዕለት ደራሽ ድጋፍ ለማድረስ እና በዘላቂነት ለማቋቋም እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የዕለት ደራሽ ድጋፍ ለማድረስ እና በዘላቂነት ለማቋቋም ከክልሎችጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ተናገሩ።
ኮሚሽነሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የክረምቱ ወቅት ከመግባቱ በፊት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ አልያም ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማስገባት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡
ተፈናቃዮች ያሉበት ርቀት፣ ከክልሎች ጋር ያለው የመረጃ ልውውጥ ክፍተት እና የጸጥታ ችግርም ለተጎጅዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ተግዳሮት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ክልሎች የራሳቸውን አቅም አጠናክረው የፌዴራል መንግስቱን ሳይጠብቁ ምላሽ የሚሰጡበት ስርዓት እስከ ወረዳ ድረስ ይዘረጋልም ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡
ተፈናቃዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም ከተለያ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም አስረድተዋል፡፡
በዚህ መሰረት ቀጣዩ ክረምት ከመግባቱ በፊት ተፈናቃዮችን ወደ ዘመዶቻቸው፣ ወደ ቀያቸው እንዲሁም ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የማስገባት ስራ ይሰራልም ብለዋል።
አጋር አካላት ለተፈናቃች እያደረጉ ያሉት ድጋፍ ቀዝቃዛ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ምትኩ ÷እስካሁን እነዚህ ለጋሽ ሀገራት ለተፈናቃዮች ያደረጉት ድጋፍ 30 በመቶ ብቻ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም ለጋሽ ሃገራት ለተፈናቃች አስፈላጊውን የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያቀርቡ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የ2021 አዲስ የተረጂዎች ቁጥር በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግም ነው የተናገሩት፡፡
በሀገሪቱ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ተመልሰው የቀደመ ህይወታቸውን እንዲመሩም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.