Fana: At a Speed of Life!

ለትምህርቱ ዘርፍ የሚመደበውን ገንዘብ በማሳደግ ጠንካራና በቴክኖሎጅ የተደገፈ የትምህርት ስርአት እንዲኖር ይሰራል – ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ኢትዮጵያ ለትምህርት ዘርፉ የምትመድበውን ገንዘብ በማሳደግ ጠንካራና በቴክኖሎጅ የተደገፈ የትምህርት ስርአት እንዲኖር ቁርጠኛ መሆኗን ተናገሩ፡፡

ዓለም አቀፉ የትምህርት ጉባኤ በበይነ መረብ አማካኝነት እየተካሄደ ሲሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በጉባኤው ላይ ሃገራት ለትምህርት ዘርፉ የሚያወጡትን በጀት እንዲያሳድጉ፣ ጠንካራ እና በቴክኖሎጅ የተደገፈ የትምህርት ስርአት እንዲኖራቸው ተጠይቋል፡፡

ኢትዮጵያም ለዘርፉ የምትመድበውን ገንዘብ በማሳደግ ጠንካራና በቴክኖሎጅ የተደገፈ የትምህርት ስርአትን ለመገንባት ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ገልጸዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊ ሃገራትም በድህረ ኮቪድ ለትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ነው የገለጹት፡፡

ጉባኤው ስለ ትምህርት ፋይናንስ፣ በኮቪድ 19 ምክንያት የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ስለመክፈት፣ የአካቶ ትምህርት፣ የመማር ማስተማር ሂደትና እና በዲጅታል ትምህርት ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል።

በጉባኤው ላይ በ2021 የዓለም የትምህርት የትኩረት መስክ ምን መምሰል እንዳለበት ቀጣይ አቅጣጫና ውሳኔ እንደሚተላለፍ ይጠበቃል፡፡

የሃገራት መሪዎች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ ሃላፊዎች፣ የትምህርት ሚኒስትሮች እና ባለድርሻ አካላት በጉባኤው እየተሳተፉ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.