Fana: At a Speed of Life!

ለአማራ ክልል ከ79 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በጦርነቱ ውድመትና ዝርፊያ ለደረሰባቸው ጤና ተቋማት ከ79 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና መሳሪያ እና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።
ድጋፉን በአሜሪካ የልማት ድርጅት የትራንስፎርም ፕራይመሪ ሄልዝ ኬር የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው ያደረገው፡፡
የትራንስፎርም ፕራይመሪ ሄልዝ ኬር ኃላፊ እና የፓዝ ፋይንደር ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር ዶክተር መንግስቱ አስናቀ እንዳሉት÷ ድርጅታቸው በጦርነቱ ውድመትና ዝርፊያ ያጋጠማቸውን ጤና ተቋማት መልሶ ለማደራጀት ከ234 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
አሁን የተደረገው የ79 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የህክምና መሳሪያዎችና የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍ የክልሉ ጤና ቢሮን ፍላጎት መሰረት አድርጎ መቅረቡን ጠቁመው÷ይህም የእናቶችን እና ህጻናት ጤናን ለማሻሻል እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
የጤና ሚኒስቴር አማካሪ ዶከተር ማርታ ምንውየለት በበኩላቸው÷ ድርጅቱ በጦርነቱ ውድመትና ዝርፊያ ለደረሰባቸው ጤና ተቋማት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጤና ሚኒስቴር ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ ለማደራጀት የተጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በጦርነቱ የወደሙና የተዘረፉ ጤና ተቋማት በመንግስትና በአጋር ድርጅቶች ርብርብ መልሶ በማደራጀት ስራ እንዲጀምሩ መደረጋቸውን አንስተዋል፡፡
ድርጀቱ ጤና ተቋማት ያለባቸውን ችግር ለይቶ ያደረገው ድጋፍ ተቋማቱን መልሶ በማደራጀት ለሚደረገው ርብርብ ጠቀሜታው የጎላ ነው ያሉት ሃላፊው ÷ሌሎች አጋር ድርጅቶችም እገዛና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.