Fana: At a Speed of Life!

ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የስራ ማስኬጃ ብድር ለማቅረብ ታቅዷል – የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት  ለአምራችኢንተርፕራይዞች 1 ነጥብ 66 ቢሊየን ብር የስራ ማስኬጃ ብድር ለማሰራጨት መታቀዱን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታወቀ፡፡

የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ አቅርቦት ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ታልሞ በተያዘው እቅድ በባንኮችና በማይክሮ ፋይናንስ አማካኝነት 1 ሺህ 591 ለሚሆኑ አምራችኢንተርፕራይዞች 1 ነጥብ 66 ቢሊየን ብር የስራ ማስኬጃ ብድር ለማሰራጨት የታቀደው፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ልማት ባንክና በሊዝ አክሲዮን ማህበራት አማካኝነት 1 ሺህ 430 ለሚሆኑ አምራች ኢንተርፕራይዞች 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ማምረቻመሳሪያዎችን ለማቅረብም ታቅዷል፡፡

ለአምራች ኢንተርፕራይዞቹ የሚቀርበው የስራ ማስኬጃ ብድር አቅርቦትና ማምረቻ መሳሪያዎች፣ አምራች ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ኤክስፖርትና ተኪ ምርቶች ላይ በብዛት መሰማራት እንዲችሉ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከክልል የዘርፉ ቢሮዎች፣ ከፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረውን ቅንጅታዊአሰራር በማጠናከርና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በፍጥነት በመፍታት ለአምራች ኢንተርፕራይዞቹ የስራማስኬጃ ብድርና የማሽን ሊዝ አቅርቦቱን ለማቀላጠፍ ታስቧል ነው የተባለው፡፡

በበጀት ዓመቱ በአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የስራእድል ፈጠራ፣ የወጪ ንግድ ስራዎችና ተኪምርትን በሀገር ውስጥ የማምረት ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩ እንደሚጠበቅ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጠናቀቀው የ2014 በጀት ዓመት 1 ሺህ 420 ለሚሆኑ አምራች ኢንተርፕራይዞች 1 ነጥብ 47 ቢሊየን ብር የሚሆን የስራማስኬጃ ብድር እንዲሁም 1 ሺህ 523 ለሚሆኑ አምራች ኢንተርፕራይዞች 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ማምረቻመሳሪያዎችን ማሰራጨት መቻሉ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.