Fana: At a Speed of Life!

ለአሰላ  የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተርባይን ከሚያቀርበው ሰይሜንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አሌክትሪክ ሀይል ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተርባይን ከሚያቀርበው ሰይመንስ ጋሜሳ ጋር ስምምነት ተፈራረመ።

100 ሜጋዋት ሀይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው የአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ በአዳማ እና አሰላ መካከል የሚገኝ ነው።

ይህ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ተመጣጣኝ ሀይል ማቅረብ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል።

በተደረሰው ስምምነት መሰረት ሰይሜንስ ጋሜሳ ለአሰላ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ኤስጂ 3 ነጥብ 4 -132 የነፋስ ተርባይኖችን ከፈረንጆቹ 2023 ጀምሮ ያቀርባል ተብሏል።

ሰይሜንስ ጋሜሳ የኢንጅነሪንግ ፣ አስፈላጊ የአገልግሎትና ምርት አቅርቦት እና የሀይል ማመንጫውን የግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ አጠናቆ የማስረክብ ሃላፊነት እንዳለበት አፍሪካ ቢዝነዝ ኮሙዩኒቲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ የሀይል ፍላጎቷን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ ከታዳሽ የሀይል ምንጭ ለማሟላት እየሰራች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ ከነፋስ 10 ጊጋዋት ሀይል ማመንጨት አቅም ያላት ሲሆን አሁን ላይ ሀገሪቱ ከነፋስ የምታገኘው ሀይል 324 ሜጋዋት መሆኑ ነው የተነገረው።

ለነፋሰ ሀይል ማመንጫው ኢትዮጵያ እና የዴንማርኩ ዳንስኬ ባንክ ግሩፕ የ117 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈራርመዋል

ከዚህ ውስጥ 94 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮው የባንኩ ግሩፕ በድጋፍ መልክ የሚሰጠው ነው።

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሲሆን 4 ነጥብ 49 ቢሊየን ብሩ ከባንኩ ግሩፕ በተገኘ ድጋፍ እና ብድር የሚሸፈን ይሆናል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

 

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

 

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

 

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.