Fana: At a Speed of Life!

በኢሚሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለአብርሆት 15 ሺህ መጻሕፍት ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላትና ምሁራን 15 ሺህ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍትና ለሦስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፉን ያደረጉትበተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በተለይም በአቡዳቢና አካባቢው የሚኖሩ ምሁራን ሲሆኑ÷ መጻሕፍቱ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍትና ለወሎ፣ ወልዲያና መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲዎች መማሪያና ማጣቀሻ እንዲሆኑ ተበርክተዋል፡፡

በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱኳን አያኖ ÷ ዳያስፖራው ሀገሩ በፈለገችው ጊዜ ሁሉ በመገኘት ፍቅሩን በተግባር እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው ÷ በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ ትምህርት ቤቶች በግጭቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት በማስተናገዳቸው ዳያስፖራው በፖለቲካ አመለካከት ሳይገደብ ማኀበረሰቡን ለማገዝ በአንድነት እንዲቆም ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ÷ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ዳያስፖራዎች ከዚህ ቀደም ሲያደርጉ የቆዩትን ድጋፍ አጠናክረው በመቀጠል በዕውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ አበርክቷቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መጻሕፍቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ወጪ እንደወጣባቸው ታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.