Fana: At a Speed of Life!

ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ 1 ሺህ ነዋሪዎች የምግብ አቅርቦት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በልደታ ክፍለ ከተማ ለእንቅስቃሴ ዝግ በሆነው አካባቢና በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ለሚገኙ 1 ሺህ ለአደጋ ተጋላጭ ነዋሪዎች ለሶስት ወር የሚቆይ የምግብ አቅርቦት ተጀመረ።

የምግብ አቅርቦቱን የደገፈው ቢልጌትስ ፋውንዴሽን መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የምግብ አቅርቦቱን በስፍራው በመገኘት አስጀምረውታል።

ኢንጂነር ታከለ ከኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር መጨመር ጋር በተያያዘ በሚከሰቱ ችግሮች ብዙዎች ችግር ውስጥ ሊወድቁ ስለሚችሉ ከመንግስት ድጋፍ ባለፈ እርስ በእርስ መረዳዳት የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ደርሰናል ብለዋል።

የምግብ አቅርቦቱ በየሁለት ቀኑ ለነዋሪዎቹ የሚከፋፈል ይሆናል ተብሏል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.