Fana: At a Speed of Life!

ለኮሮና ቫይረስ ሃገር በቀል ህክምናን ከዘመናዊው ጋር በማጣመር መድሃኒት እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኮሮና ቫይረስ የሃገር በቀል የባህል ህክምና አዋቂዎችን ከዘመናዊው ጋር በማጣመር መድሃኒት እየተዘጋጀ መሆኑ ተገለጸ።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስን በሳይንሳዊ ምርምር በተደገፈ የሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ለማከም የተሰራው መድሃኒት መሰረታዊ የምርምር ሂደት አልፎ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሂደቶች ማለፉን መግለጹ ይታወሳል።

አሁን ላይም ምርምሩ ተደጋጋሚ የምርመር ሂደት አልፎ ወደ ምርት እና ቀጣይ የእንስሳት እና ክሊኒካል ፍተሻ ስራዎች እንዲሸጋገር መደረጉንም ነው የገለጸው።

በጉዳዩ ላይ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን፥ ዓለም ላይ ከሚገኙ 8 ሺህ በላይ እፅዋቶች 7 ሺህ በኢትዮጵያ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።

በመሆኑም ቀደም ሲል ባህላዊውን ከዘመናዊው ጋር አጣምሮ የመስራቱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተነሳ ሲሆን፥ አሁን ለተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የሚሆን መድሃኒት ባህላዊውን ከዘመናዊው ጋር አጣምሮ የመፈለጉ ስራ ተጠናክሮ ተስፋ ሰጭ ሁኔታ እየታየ ነው ተብሏል።

የመድሃኒቶቹ ፍለጋ የዓለም ጤና ድርጅትና የኢትዮጵያን መስፈርቶች በማሟላት ዝግጅት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝም ነው በመግለጫው የተነሳው።

የመድሃኒቶቹ ዝግጅት ተጠናቆ ሲገኝ በጤና ሚኒስቴርና በኢኖቬሽንና ቴክኖሌጅ ሚኒስቴር በኩል ይፋ እንደሚሆንም ተገልጿል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.