Fana: At a Speed of Life!

ለዘማች የመገናኛ ብዙሀንና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ“ዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” ወቅት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ዘማች የመገናኛ ብዙሀንና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ዛሬ እውቅና ተሰጥቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም ባለሙያዎቹ ያበረከቱትን አስተዋጽዖ አስመልክቶ ለማመስገን በተዘጋጀው ስነ-ስርዓት ላይ ለዘማች የመገናኛ ብዙሀን እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እውቅና ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በእውቅና መስጠት መርሃ ግብሩ ላይ ለዘማች የመገናኛ ብዙሃን እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች  ባስተላለፉት መልዕክት፥ ስለጦርነትና ስለተገኘው ድል ኮራ ብሎ ለመናገርና ለመግባባት የሚያስችለው ትክክለኛው ስብስብ የዛሬው ነው ብለዋል።

“በቅርበት ጉዳዩን የመራ፣ የተራበ፣ ያበረታ፣ያከመ ስብስብ ነው፤ እናንተ ያሸነፋችሁት በንግግር ሳይሆን በተግባር ነው” ብለዋል።

“እስካሁን ካገኛችሁት ድል እና ውጤት የላቀ ድካምና ስራ ከፊታችሁ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

በድል ማግስት ትልቁ ነገር የአሸናፊነት ስነልቦና ተሸክሞ ራስን ማሸነፍ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በመሆኑም “እናንተ አሸናፊዎች ራሳችሁን ማሸነፍ ካልቻላችሁ ድሉ ይበላሻል” ነው ያሉት።

“አሸናፊ ራሱን የሚገዛበትና ስሜት ከሌለው ያስገኘውን አመርቂ ውጤት ሊያበላሽ ይችላል። ይህም እንዳያጋጥም መጠንቀቅ ይኖርብናል” ሲሉ መክረዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.