Fana: At a Speed of Life!

ለጊቤ ወንዝ – ጅማ መንገድ ከባድ ጥገና እየተደረገለት ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰትን በማስተናገድና በአገልግሎት ብዛት ለጉዳት የተዳረገው የጊቤ ወንዝ – ጅማ መንገድ ከባድ ጥገና እየተደረገለት ነው።

167 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የጊቤ ወንዝ – ጅማ መንገድ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በጅማ ዲስትሪክት የከባድ ጥገና ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የዲስትሪክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ደመቀ የጊቤ ወንዝ – ጅማ መንገድ ከሚሰጠው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ አኳያ ከባድ ጥገና ማድረጉ ወሳኘ በመሆኑ ስራው መጀመሩን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከ60 ሚሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለት በራስ ሀይል የከባድ ጥገና ስራው በጥሩ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በመንገድ ፕሮጀክቱ ውስጥ በእጅጉ የተጎዳውን የመንገድ ክፍል በቅድሚያ ጥገናውን በማከናወን የትራፊክ ፍሰቱ ምቹ እንዲሆን እየተደረገ ነው ተብሏል።

የጊቤ ወንዝ – ጅማ መንገድ የአዲስ አበባ – ጅማ- ቦንጋ ሚዛን የመንገድ አንዱ ክፍል መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በየአካባቢዎቹ የሚመረተውን ከፍተኛ የቡና ምርትን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ውጤቶችን ወደ መሀል ሃገር በማድረስ አምራችና ሸማችን በሰፊው ተጠቃሚ ያደርጋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.