Fana: At a Speed of Life!

ለግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮች የኃይል አቅርቦት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተለያየ የሀገሪቱ ክፍል ለተገነቡት የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች የኃይል አቅርቦት መሰረተ ልማት ለመዘርጋት የሚያስችል ስምምነት ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ፡፡

ሲኖ ሀይድሮ እና ሲዩአን ኤሌክትሪክ ከተሰኙ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር ነው የተፈረመው፡፡

ስምምነቱ ለቡሬ፣ ለበአከር፣ የወይናንታ እና የገንዳ አርባ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ለዳንሻ፣ ሁመራ፣ ጎንደር II ማከፋፈያ ጣቢያዎች የዲዛይን፣ የዕቃዎችን ፍብሪካና አቅርቦት፣ የግንባታ እንዲሁም የሙከራና ፍተሻ ሥራዎችን ያጠቃልላል ተብሏል፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የየኩባንያዎቹ ተወካዮች ተፈራርመዋል፡፡

አቶ አሸብር ባልቻ መንግስት የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ስምምነቱ ለኢንዱስትሪ ፓርኮቹን የኃይል ጥያቄ ለመፍታት ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የፕሮጀክቶችን ሥራ በጥራትና በተቀመጠላቸው መርሃ ግብር  መሰረት አጠናቆ ለማስረከብ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

የቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክትን በ14 ወራት ውስጥ በማጠናቀቅ ለማስረከብ እና ከ15 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይና ከ118 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መመደቡን አቶ ሁሴን ተናግረዋል፡፡

አቶ ሁሴን አክለውም ለጎንደር II፣ ለዳንሻ፣ ለበአከርና ለሁመራ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ የሚዉለውን ዕቃ ለማቅረብ የተካሄደው ስምምነት ከ10 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር በላይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይ ከሲኖ ሀይድሮ ኩባንያ ጋር የተካሄደው ስምምነት በምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ አካባቢ ለሚገነባው የገንዳ አርባ እና በይርጋለም አካባቢ ለተገነባው የወይናንታ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርክ ባለ 132/33 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያ የዲዛይን፣ የፍብረካና አቅርቦት፣ የግንባታ እንዲሁም የሙከራና የፍተሻ ስራዎችን ለማከናወን ነው፡፡

የገንዳ አርባንና የወይናንታን የማከፋፈያ ጣቢያዎችን ፕሮጀክት በ12 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እና ለዚህም ከ13 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላርና ከ14 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ስምምነት መደረጉን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

ለሁሉም ፕሮጀክቶች የሚያስፈልገው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.