Fana: At a Speed of Life!

ለግድቡ በ8100 ከ88 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ባለፉት ስምንት ወራት በ8100 የሞባይል አጭር ጽሁፍ መልዕክት ከ88 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ተገለጸ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ አብርሃም ነው ያስታወቁት።

በኢትዮ ቴሌኮም ጥቅል አገልግሎት ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጉ አዲስ ፕላትፎርም ይዘጋጃልም ተብሏል፡፡

ግድቡ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በህብረተሰቡ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮ ቴልኮም ጥቅል አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለህዳሴ ግድብ ቢልኩም ከሂሳባቸው አይቀንስም ተብሎ ለተነሳው ጉዳይ አቶ ኃይሉ ችግሩ መኖሩን አምነው አሁን ያለው ፕላትፎርም የሞባይል ጥቅል አገልግሎትን አያስተናግድም ብለዋል፡፡

ጥቅል አገልግሎትን ለማስተናገድ ሶፍትዌሩ እና ተያያዥ ጉዳዮች ጊዜ የሚወስዱ በመሆናቸው ችግሩ እስከሚቀረፍ ድረስ ካርድ በመሙላት የተለመደውን ድጋፍ ህብረተሰቡ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ የተከሰተውን ጉዳይ እንደሚያውቀውና እና በቀጣይ ወራት ችግሩን ለመቅረፍ ከተቋሙ ጋር እየሰራ መሆኑንም ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.