Fana: At a Speed of Life!

ለጤና ሚኒስቴር 30 ሚሊየን ብር የሚወጣ ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጤና ሚኒስቴር የኮቪድ- 19ን ለመከላከልና የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ 30 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 100 ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ ተደረገ፡፡
 
ድጋፉን የሞደርን ኢ.ቲ.ኤች አውት ሶርስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ተወካይ አቶ ታዲዮስ ተፈራ ለጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስረክበዋል፡፡
 
ተወካዩ ድጋፉ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ዜጎችን ለመርዳት ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልጸው÷ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
 
ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ÷ መሳሪያዎቹ በጽኑ ህሙማን ማገገሚያ የሚገኙ ታካሚዎችን ለመርዳት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
 
ሚኒስትሯ ማህበሩ በቀጣይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
 
የህክምና መሳሪያዎቹን ድጋፍ ያደረጉ እና እቃዎቹን ወደ ሀገር ቤት በማጓጓዝ ያስረከቡ ድርጅቶች ከጤና ሚኒስቴር የምስጋና የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.