Fana: At a Speed of Life!

ለፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር ሊለማለት ነው

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለፋሲል ከነማ የስፖርት ክለብ ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር ሊለማለት ነው።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደሩ የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድንን መረጃ ለደጋፊዎቹና ለማህበረሰቡ ባሉበት ለማድረስ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አህመዲን መሐመድ፥ ከፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ስራ አስኪያጅና የቦርድ አመራሮች ጋር ቡድኑን የዲጂታል ፖርታል ባለቤት ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደሩ ከፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ሊንክድኢን ከመሳሰሉ ማህበራዊ ሚዲያዎችና ከቴሌ ብር ጋር በማገናኘት አገልግሎት መስጠት የሚያስችልም ነው።

የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር በአንድ ወር ጊዜ አልምተው እንደሚያስረክቡ ዶክተር አህመዲን መሐመድ ገልጸዋል።

እንደ ሀገር የተጀመረውን የዲጂታል ጉዞ ወደ ሁሉም ዘርፎች ለማውረድ ይሰራልም ብለዋል።

የፋሲል ከነማ የስፖርት ቡድን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዮት ብርሃኑ በበኩላቸው÷ ባለሙያዎችን በማሟላት የመረጃ አስተዳደሩ ሳይቆራረጥ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዲጂታል የመረጃ አስተዳደር ስርዓቱ የክለቡን ታሪክ፣ ዕለታዊ የእንቅስቃሴ መረጃ፣ የገቢ ማስገኛ ሽያጭ፣ የደጋፊዎች መረጃ፣ ድጋፍ ማሰባሰቢያና የመሳሰሉትን መረጃዎች አስተሳስሮ እንደሚይዝ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.