Fana: At a Speed of Life!

ለ20ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት ጥሪ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ከ20ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ አቻው በመስከረም ወር ላለበት ጨዋታ አሰልጣኝ ፍሬው ኃ/ገብርኤል ለ40 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው የብሔራዊ ቡድኑ አባላትም ከአዲስ አበባ ከተማ ቤተልሔም ታምሩ ፣ አብነት ለገሰና በሻዱ ረጋሳ ሲሆኑ ÷ከአዳማ ከተማ ናርዶስ ዘውዴና እየሩሳሌም ሎራቶ ናቸው፡፡
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አረጋሽ ካልሳ፣ ታሪኳ ዲቤሳ፣ ትዕግስት ሀይሌ ፣ ብዙአየሁ ታደሰና ፎዚያ መሐመድ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ አርያት ኦዳንጎ፣ የምስራች ሞገስና ንግስት በቀለ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከድሬ ዳዋ ከተማ ደግሞ ጸጋነሽ ወላና፣ ማዕደን ሳህሉ ፣ ብርቄ አማረ ፣ ቤቲ ዘውዴ ፣ትሁን አየለና ፍሬወይኒ አበራ ሲሆኑ ከባህር ዳር ከተማ ባንቺአየሁ ደመላሽና ከአርባ ምንጭ ከተማ መስከረም ኢሳያስ ጥሪ ተደገርጎላቸዋል፡፡
እንዲሁም ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ዮርዳኖስ ሙዝ ፣ ፋና ዘነበ ፣ሲሳይ ገ/ህዋት ከቅዱስ ጊዮርጊስ እየሩሳሌም ወንድሙ፣ንግስት አስረስ ከቦሌ ክፍለ ከተማ መአዛ አብደላ ከአቃቂ ቃሊቲ ማክዳ አሊና ሄለን መሰለ ከመከላከያ ስፖርት ክለብ ገነት ሀይሉ ፣ ቤቲ በቀለ፣ ነፃነት ፀጋዬ ፣ መሳይ ተመስገንና ኤልሳቤት ብርሃኔ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡
ከዲላ ከተማ ደግሞ ቱሪስት ለማ፣ ፀገነት ግርማና መስከረም መንግስቱ እንዲሁም ከሐዋሳ ከተማ ረድኤት አስረሳኸኝ ፣ አይናለም አሳምነውና አባይነሽ አርቂሎ ናቸው ጥሪ የተደረገላቸው፡፡
ጥሪ የተደረገላቸው የብሔራዊ ቡድኑ አባላትም ዝግጅታቸውን ከነሀሴ 21 ቀን 2013ዓ.ም ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚያከናውኑ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.