Fana: At a Speed of Life!

ለ50 ሺህ ከስደት ተመላሽ ሴቶች የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር ፕሮጀክት ተጀመረ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአንድ አመት ውስጥ ለ50 ሺህ ከስደት ተመላሽ ሴቶች የሥራ ዕድሎችን የሚፈጥር ፕሮጀክት ተጀመረ።

የኢፌዴሪ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከጃምቦ የጽዳት አገልግሎት ጋር ለከስደት ተመላሽ ሴቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ለማስጀመር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

ፕሮጀክቱ ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሚመለሱ ሴቶች በጽዳት፣ በምግብ ሥራና የቤት ለቤት አገልግሎቶች በመሰማራት ገቢ የሚያገኙበትን ስርዓት ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር የሚተገበር ነው።

እነኚህ ሴቶች በሌሎች አገራት በሚሰሩባቸው የሥራ ዘርፎች ተግባራዊ ልምድ ያካበቱና ሠርተውም ገቢ የሚያገኙ እንዲሁም ለአገር ኢኮኖሚ ገንዘብ በመላክ አስተዋጽዖ ሲያደርጉ የነበሩ ስለሆኑ በቀላሉ ወደሥራ ለመግባት የሚችሉ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢፌድሪ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከስደት ተመላሽ ሴቶችን ወደ ሥራ ማሰማራት ያለውን ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊያና ስነልቦናዊ ጠቀሜታ እንዲሁም ተመሳሳይ ተግባራት ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ የግሉ ዘርፍ አካላት መልካም ተሞክሮ ነው ብለዋል።

በፕሮጀክቱ የሚካተቱ ሴቶች በቅድሚያ የ16 ቀናት የስነልቦና ዝግጁነት፣ የብቁ ባለሙያነት፣ ጠቅላላ የጽዳት ሥራና የምግብ ዝግጀት ማጎልበቻ አጭር ስልጠናዎችን የሚወስዱ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelev

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.