Fana: At a Speed of Life!

ሊባኖስ ለቤይሩት ፍንዳታ ምክንያት የሆነውን ኬሚካል በግዴለሽነት ያስቀመጡ ባለስልጣናት በቁም እስር እንዲቆዩ ትእዛዝ ሰጠች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 30፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ሊባኖስ ከትናንት በስቲያ በቤይሩት ለደረሰው ፍንዳታ ምክንያት የሆነውን ኬሚካል በግድየለሽነት እንዲከማች ያደረጉ ባለስልጣናት በቁም እስር ላይ እንዲቆዩ አዘዘች።

መርማሪዎች ተቀጣጣይ ኬሚካሉ በግዴለሽነት በመጋዘን ውስጥ መከማቸቱ ላይ ትኩረት አድርገው የአደጋውን መንስኤ እያጣሩ ይገኛሉ።

በርካቶችም በመጋዘኑ በግዴለሽነት ተከማችቷል የተባለው 3 ሺህ የሚጠጋ አሞኒየም ናይትሮጂን የተባለ ኬሚካል የፍንዳታው መንስኤ መሆኑን ያምናሉ።

በፍንዳታው እስካሁን 135 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን፥ 5 ሺህ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በተጨማሪም 300 ሺህ ሰዎች በዚህ አደጋ ከቤታቸው መፈናቀላቸው ነው የተመለከተው።

የደረሰው ኢኮኖሚያዊ ኪሳራም ከ10 ቢሊየን እስከ 15 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.