Fana: At a Speed of Life!

ላለፉት ሳምንታት በሪያድ ፖሊስ ጣቢያዎች የቆዩ 82 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያን የመኖሪያ ፈቃድ ተላልፈዋል በሚል ላለፉት ሳምንታት ከልጆቻቸው ጋር ተይዘው ሪያድ ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች የቆዩ 82 ዜጎች እንዲፈቱ ተደረገ።

እነዚህ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በከተማው ውስጥ በሚገኙ አምስት ፖሊስ ጣቢያዎች በጊዜያዊነት ከሶስት ሳምንታት በላይ እንዲቆዩ ተደርገዋል፡፡

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዳስታወቀው ከሚመለከታቸው የሀገሪቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ዜጎቹ እንዲፈቱ ተደርጓል፡፡

ከቤተሰቦቻቸው ጋር ታስረው የነበሩ ህፃናትም የህክምና ክትትል እና ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉንም አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.