Fana: At a Speed of Life!

ልጇን ከተገላገለች ከሰዓታት በኋላ  የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና የወሰደችዉ ተማሪ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ተማሪ ጌጤ ናደዉ ልጇን ከተገላገለች ከሰዓታት በኋላ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለመግባት የሚያስችላትን ፈተና  ወስዳለች።

ተማሪ ጌጤ ናደዉ በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ነዋሪ  ነች።

በ2010 ዓ.ም የመሰናዶ ትምህርቷን ጨርሳ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችል ዉጤት  ባይመጣላትም÷ በሁኔታዎች ተስፋ ያልቆረጠችዉ ጌጤ ድጋሚ በግል ለመፈተን ቅድመ ዝግጅት አድርጋ ብትጠባበቅም ኮሮና ቫይረስ ፈተናዉ እንዲዘገይ ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህ መሀል ነፍሰ ጡር የነበረችዉ ወይዘሮ ጌጤ ናደዉ÷የ2013 ሀገር አቀፍ ፈተና ሰኞ ሊጀመር እሁድ ልጇን በሰላም ተገላግላለች፡፡

አራሷ ጌጤ የግል ተፈታኝ ሆና ከሰኞ እስከ ሀሙስ የተሰጠዉን ሀገር አቀፍ ፈተና በፅናት ጨርሻለሁ ስትል ለሚዛን አማን ፋና ገልጻለች፡፡

በደቡብ ክልል ከ30ሺህ 81 ተማሪዎች የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ወስደዋል፡፡

በተስፋዬ አይጠገብ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.