Fana: At a Speed of Life!

መሪዎች የውሃ አካላትን ደኅንነት ለመጠበቅ በተደረሰው ስምምነት ላይ ሊወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተመድ አባል ሀገራት የውቅያኖስ እና የባሕር ሥነ-ሕይወትን ለመንከባከብ እና ከብዝበዛ ለመታደግ ተጨማሪ ውይይት ለማካሄድ በኒውዮርክ እንደሚሰበሰቡ ተገልጿል።

በስብሰባቸው ሥምምነት ላይ ከደረሱ 30 በመቶ ያህሉ የዓለማችን የውቅያኖስ ክፍል በ2030 ጥበቃ እንደሚደረግለት ተመላክቷል፡፡

የውሃ ሥነ-ሕይወት ተሟጋቾች ÷ ሥምምነቱ ከተፈረመ ዓሳ የማስገር እና ሌሎችን ሥነ-ሕይወትን የሚጎዱ ተግባራት ላይ ገደቦች ይጥላል በሚል ተሥፋ ሰንቀዋል፡፡

ባሳለፍነው መጋቢት ወር ላይ ሀገራት ሥምምነቱን ለመፈረም የመጨረሻ እና አምሥተኛውን ስብሰባቸውን ለማድረግ ተስማምተው መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

ሀገራቱ እስከ ዓመቱ መጨረሻም ቀነ-ገደብ አስቀምጠው ለመፈረም መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

እንደሚታወሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መሪዎች በውሃ አካላት ሥነ-ሕይወት ጥበቃ ላይ ላለፉት 10 ዓመታት ድርድር ሲያደርጉ ቢቆዩም ሥምምነት ላይ ደርሰው የተፈራረሙበት ሠነድ እስካሁን የለም፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.