Fana: At a Speed of Life!

መስፈርቱን ሳያሟሉ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እናደርጋለን የሚሉ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኢንስቲትዩቱ አሳሰበ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መስፈርቱን ሳያሟሉ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እናደርጋለን የሚሉ ተቋማት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

ኢንስቲትዩቱ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የላብራቶሪ ማስፋፊያን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በተሠራው የላብራቶሪ ማስፋፊያ ሥራም ከአንድ ላብራቶሪ ምርመራ ተቋም በመነሳት በምርምር ተቋማት፣ በክልል ላብራቶሪዎች፣ በዩኒቪርቲዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት ጋር በመተባበር የኮቪድ-19 ምርመራ ተቋማትን ማስፋፋቱን ጠቅሷል።

በዚሁ መሰረት የግል ተቋማት አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ በኋላ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ፍቃድ እንደሚሰጣቸው ነው የገለጸው።

ይህንን ፍቃድ ካገኙ 15 የግል ተቋማት 13 ነባር የግል ተቋማት መሆናቸውን እና 2 አዲስ መስፈርቱን አሟልተው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እና የውጤት የሰርተፊኬት የሚሰጡ የግል ተቋማት በሥራ ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ይሁን እንጂ በቅርቡ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እናደርጋለን፤ እስከ 6 ሰዓትም ውጤት እናሳውቃለን እያሉ ማስታወቂያ የሚያሰራጩ ተቋማት መኖራቸውን የደረሰበት መሆኑን አስታውቋል።

ስለሆነም ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ ምርመራ እናደርጋለን የሚሉ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ ማኅበረሰቡም መስፈርቱን አሟልተው እውቅና በተሰጣቸው ተቋማት ብቻ አገልግሎት እንዲያገኙ አሳስቧል።

አዲስ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋማት ሲኖሩ የሚያሳውቅ እንደሆነም ነው የገለጸው።

መስፈርቱን አሟልተው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ የሚሰጡ የግል ተቋማትን በዝርዝር አስቀምጧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.