Fana: At a Speed of Life!

መቐለ ከተማ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ወደ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር በዋለችው መቐለ ከተማ በተወሰነ መልኩም ቢሆን የሰዎች እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

የጋዜጠኞች ቡድን በዛሬው ዕለት በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ቅኝት አድርጓል።

በዚህም በተወሰነ ደረጃ እንቅስቃሴ እየተመለሰች በምትገኘው መቐለ ከተማ ተዘግተው የቆዩ ሱቆችም በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች መከፈታቸውን በስፍራው የሚገኘው ባልደረባችን ባደረገው ቅኝት መታዘብ ችሏል፡፡

አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች “የምንፈልገው ሰላም ነው፤ የተቋረጡ የመብራትና የስልክ አገልግሎት ይመለሱልን” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

አሁን ላይም ሰራዊቱ ከህግ ማስከበር ዘመቻው ውጭ ምንም አይነት ተፅዕኖ እንዳልፈጠረባቸውም ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል ሲያካሂድ የነበረውን ህግን የማስከበር እርምጃ መቐለ ከተማን በቁጥጥር ስራ ካዋለ በኋላ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው።

አሁን ላይ በተለያዩ ወንጀሎች የሚፈለጉ አካላትን የማፈላለግ ስራ ነው እየተወከናወነ የሚገኘው።

በፋሲካው ታደሰ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.