Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ህግን ማስከበርና ዜጎችን የመጠበቅ ግዴታ ስለነበረበት ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ ገብቶ ነበር – አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ መንግስት ህግ ማስከበርና ዜጎችን የመጠበቅ ግዴታ ስለነበረበት ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ ገብቶ እንደነበር ገለጹ፡፡

አምባሳደር ሄኖክ “አይ ኦን አፍሪካ” በሚሰኘው ፕሮግራም ከፍራንስ 24 የቴሌቪዝን ጣቢያ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በነበራቸው ቆይታም በሰሜን ዕዝ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ እየተካሄደ የነበረው ህግ የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት መንግስት የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው እንዲመለሱ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ነው ያስረዱት።

እንዲሁም በጁንታው ቡድን አማካኝነት የወደሙ የመሰረተ ልማት አውታሮች ወደ አገልግሎት እንዲገቡ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

አምባሳደር ሄኖክ በመንግስት ቁጥጥር ውስጥ በሚገኙ ቦታዎች የሚኖሩ ዜጎች ድጋፍ እያገኙ መሆኑን ነው በቆይታቸው ያስረዱት።

እንዲሁም መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪዎች ጋር በመሆን በትብብር እየሰራች መሆኑን ከፍራንስ 24 በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.