Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ለትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መንግስት ለትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።

በዚህ ስራም ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራ እንዳለም አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚነስቴር እንዳስታወቀው 70 በመቶ የሚሆነውን የሰብአዊ ድጋፍ መንግስት እያቀረበ ሲሆን 30 በመቶ የሚሆነውን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የልማት አጋሮች እየሸፈኑ ነው።

እስካሁን በተደረገው የድጋፍ አቅርቦት ከ3 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎችን መድረስ መቻሉን ነው የገለጸው።

ክልሉ እየተረጋጋ በመሆኑ ለሴቶች እና ለህጻናት ቅድሚያ በመስጠት ሲሰራ የነበረውን የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በተሻለ መልኩ ለማስፋት እየተሰራ ነውም ብሏል።

የአለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባዝሌይ በክልሉ ስላለው ሁኔታ በሰጡት መግለጫ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱ አበረታች መሆኑን መግለጻቸው አይዘነጋም።

ዓለም አቀፍ አካላትም ይህንን መነሻ በማድረግ ስራውን ከማበረታታት እና ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ ከእውነታ የራቀ ዘገባ ማቅረባቸው እና ያለአግባብ ማላዘናቸው ተገቢ አይደለም ነው ያለው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

በክልሉ ስላለው የሰብአዊ መብት ጉዳዮችም መንግስት ህገወጦችን ለህግ ለማቅረብ እና ከሚመለከታቸው አለም አቀፍ ተቋማት ጋር ለመስራት ፈቃደኛ መሆኑን ገልጿል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ጄ ብሊንከን ትናንት የሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የገባ እና አግባብነት የሌለው ነው ብሏል።

በውስጥ ጉዳይ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር በሀገሪቷ ህገመንግስት መሰረት አሰራር አለው ሲልም ገልጿል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው።

በመሆኑም በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እና እውነታን ያላገናዘበ መረጃ መስጠት ትክክል አይደለምም ብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.