Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ማንኛውንም አይነት ፆታዊ ጥቃት አይታገስም- ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ማንኛውንም አይነት ፆታዊ ጥቃት እንደማይታገስ የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ።

ሚኒስትሯ ከመከላከያ ሚኒስቴር የሴቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ጥሩዬ አሰፌ ጋር መክረዋል።

በዚህ ወቅትም በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃቶች ተፈፅሟል የሚል የተነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

ጉዳዮን ለማጠራት የተቋቋመውን ግብረ ሀይል አስመልክቶ ውይይት የተደረገ ሲሆን ግብረ ሀይሉ የሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር  ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግን እና መከላከያ ሰራዊትን ያካተተ ነው።

ግብረ ሀይሉም እውነተኛው ነገር ለማወቅ ምርመራ እና የማረጋገጥ ስራ እንደሚያከናውን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.