Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን አጠናቆ ወደ ልማት ስራው እንዲመለስ ትብብራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን – በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች

አዲስ አበባ ፣ህዳር 23 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት የህግ ማስከበር ስራውን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ወደ ልማት ስራው እንዲመለስ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ የትግራይ ተወላጆች ÷ ህገ-ወጡ የህወሓት ጁንታ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመው የክህደት ተግባር የትግራይን ህዝብ የማይወክል ነው ብለዋል፡፡
ህገ-ወጡ የህወሓት ቡድን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተጋብቶ እና ተዋልዶ ለዘመናት የኖረውን ትግራዋይ ከወገኖቹ ለመነጠል ያደረገው በመሆኑ በፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
የትግራይ ህዝብ ባለፉት 30 ዓመታት በኑሮው ላይ የተሻለ ለውጥ ሳያገኝ ይባስ ብሎ በህወሓት ቡድን መዋጮ ሲመዘበር እና ሲማረር እንደነበር ገልጸው ÷ለትግራይ ልማት መዋጮ እየተጠየቀ ብር ሲሰበሰብ ቢኖርም የተሰራው ልማትና ህዝባዊ አገልግሎት ግን እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑን ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡
የትግራይ ህዝብ ምንጊዜም ድጋፉ ለሀገሩ ኢትዮጵያ እንጂ ለህወሓት ቡድን አለመሆኑን ጠቁመው÷ ተወላጆቹ መንግስት የህግ ማስከበር ስራው በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ ልማት ስራው እንዲመለስ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የገለጹት ፡፡
መንግስት ህገ-ወጦችን ወደ ህግ ለማቅረብ ከሚሰራው የህግ ማስከበር ስራ ለንጹሃን ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ከማድረስ በተጨማሪ ከሃዲው የጁንታ ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ ለመንግስት እጃቸውን እንዲሰጡ ማሳሰባቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.