Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሀገሪቱን ለመታደግ እየወሰደው ያለውን ዕርምጃ የጋምቤላ የክልል እንደሚደግፍ አቶ ዑሞድ ኡጁሉ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ሀገሪቱን ለመታደግ እየወሰደው ያለውን ዕርምጃ የጋምቤላ የክልል እንደሚደግፍ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዑሞድ ኡጁሉ አስታወቁ።

ሕወሓት በሠራዊቱ ላይ ያደረሰው ጥቃት የሀገር ክህደት ወንጀል መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል፡፡

ይህ ድርጊትም በፅኑ ሊኮንን ይገባዋል ያሉት አቶ ዑሞድ፤ የፌዴራል መንግሥት በሕወሓት ላይ የጀመረውን ሕግ የማስከበር እርምጃ አጠናከሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በጋምቤላ ክልል ያሉ የፀጥታ አካላት የሕዝብን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እንዲወጡም መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ ሕዝቡም ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ሰላሙን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.