Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሰራዊት ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጠረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መላውን የጸጥታ ኃይል ራሳቸው በመምራት የህልውና ዘመቻውን ከዳር ለማድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል በገቡት መሠረት በግንባር ተገኝተው ቃላቸውን ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን አስታወቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተነቃቃው ጀግናው ሠራዊታችን በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሲደረግ በነበረው ውጊያ ካሳጊታን አስቀድሞ ከአሸባሪው ሕወሓት ነጻ ያወጣ ሲሆን ወደፊት በመገሥገሥ ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ እና ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው ብሏል።

በአፋር ክልል፣ በጭፍራ ግንባርም ጪፍቱን፣ የጭፍራ ከተማንና አካባቢውን ከወራሪው ነጻ አውጥቶ ወደፊት በመገሥገሦ ላይ ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.