Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙሃን ግጭት እንዳይፈጠር ሙያዊ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል-የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 7 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት መገናኛ ብዙሃን የጋዜጠኝነት ስነምግባር ደንብን በማክበር ግጭት እንዳይፈጠር ሙያዊ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ  እንደሚገባ ገለጸ።

ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ  የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ እንዳሳዘነው ገልጾ÷ግድያውን ተከትሎ የሚዲያ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች ወይም ሃሳቦችና እውነታዎች በተገቢው ሁኔታ ከተረጋገጡ በኋላ መቅረብ አለባቸው ብሏል።

ምክር ቤቱ አያይዞም ትኩረታቸውም የጋዜጠኝነት  ስነ ምግባርን እና የህግ ክልከላዎችን ባማከለ ሁኔታ የህዝቦችን ትስስር ፣ወዳጅነትና ሰላምን ለማስፈን በሚያስችል መልኩ ሊሆን ይገባልም ነው ያለው።

ምክር ቤቱ አክሎ በተለይም በህዝቦች መካከል የግጭት ስሜቶችን ሊፈጥሩ የሚችሉ  ፎቶግራፎችንና ምስሎችን ከማሳተም ወይም ከማሰራጨት መታቀብ እንዳለባቸውም ነው ያሳሰበው።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.