Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ለደብረ ብረሃን ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 20 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ለደብረ ብርሃን ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሃኪም ግዛው ማስተማሪያ ሆስፒታል 20 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አስረክቧል፡፡
 
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የተደረገው ድጋፍ የህክምና መሳሪያዎችን፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ ምግብ ነክ ግብዓቶች፣ መድሃኒቶች እንዲሁም የህጻናትና ሴቶች አልባሳትን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ድጋፉ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የቀረበ መሆኑን የገለጽት ሚኒስትሯ÷ይህም በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱ ዜጎች ለመርዳት እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡
 
አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች የጤና ተቋማትን በማውደም በጤናው ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ዶክተር ሊያ አንስተዋል፡፡
 
በሁለቱ ክልሎች የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ነው ያሉት፡፡
 
ድጋፉን የተረከቡት የደብረ ብርሃን ኮንፕርሄንሲቭ ሰፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አስማረ ሳሙኤል በበኩላቸው÷ ሚኒስቴሩ ሆስፒታሉ ያለበትን ጫና ተርድቶ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
አሁን ላይም ሆስፒታሉ ከፍተኛ የሰው ሃይል፣ የህክምና መሳሪያዎችና የመድሃኒት እጥረት ያለበት በመሆኑ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
 
በእታገኝ መኮንን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.