Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የኮቪድ19ኝን ተፅዕኖ ለመቋቋም ለአቅመ ደካሞችና ጧሪ ለሌላቸው አረጋውያን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የኮቪድ 19ኝን ተፅዕኖ ለመቋቋም እንዲረዳ ለአቅመ ደካሞችና ጧሪ ለሌላቸው አረጋውያን ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ የተደረገው በአራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ሲሆን የምግብ እህል፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስና አልባሳትን ያካተተ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች ወጪ የተሸፈነ ነው ተብሏል።

የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ደጋፉን ለክፍለ ከተማው ወረዳ 9 አስተዳደር ሃላፊዎች ባስረከቡበት ወቅት የሀገር አቀፉ የማዕድ ማጋራት ጥሪ አካል የሆነው ድጋፍ ቀጣይነት እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የወረዳ አስተዳደሩም ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናውን በማቅረብ ድጋፉን በችግር ውስጥ ላሉና ለተለዩ 200 አባወራዎች እንደሚያከፋፈል አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የትምህርት ዘርፉ የ500 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ረቡዕ በይፋ እንደሚጀመር ሚኒስትሩ መግለፃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.