Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት በ10 ዓመቱ ዕቅድ ማካተቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት በ10 ዓመቱ ዕቅድ መካተታቸውን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የዘርፉን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ እና የ2013 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች ጋር በደብረብርሀን ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ባለፉት ዓመታት የማምረቻ ዘርፉን ለማሳደግ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸውን ገልጸው ተስፋ ሠጭ ውጤቶች መኖራቸውን አመላክተዋል፡፡

በተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮች ሳቢያ ዘርፉ የተፈለገውን ያህል አንዳልተራመደ የተናገሩት ሚኒስትሩ ችግሩ አፋጣኝ እልባት የሚሻ በመሆኑ የ10 ዓመቱ መሪ ዕቅድ ይህንኑ ታሳቢ ያደረገና ችግሮችን በመቅረፍ ትርጉም ያለው ስራ ለመስራት ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት በ10 ዓመቱ ዕቅድ ላይ መካተታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለተግባራዊነቱም ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራርና ሰራተኛ እንዲሁም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይገባቸዋል ማለታቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.