Fana: At a Speed of Life!

ማሊ ከሩሲያ ሄሊኮፕተሮችን እና የጦር መሳሪያዎችን ተረከበች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማሊ ከሩሲያ ፌዴሬሽን የገዛቻቸውን አራት ሄሊኮፕተሮች እና የጦር መሳሪያዎች መረከቧን የአገሪቱ ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።
የሄሊኮፕተሮቹ፤የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶቹ ርክክብ የተካሄደው በማሊ እና በዋና ወታደራዊ አጋሯ ፈረንሣይ መካከል የሻከረ ግንኙነትና ዉጥረት በተፈጠረበት ወቅት ነዉ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
ፈረንሳይ በበኩሏ ማሊ ከሩሲያዉ ዋግነር ኩባንያ ጋር ስምምነት መፍጠሯ አገሪቱን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትገለል የሚያደርግ እኩይ ተግባር ነው ስትል ማሊን አስጠንቅቃለች።
ጊዜያዊ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሳዲዮ ካማራ በበኩላቸው፥ የጦር መሳሪያዎቹ የተገዙት የአገሪቱን ወታደራዊ አቅም ለማጠናከር አምና በሁለቱ አገሮች መካከል በተደረሰው ስምምነት መሰረት መሆኑን ጠቁመው፥ ከፈረንሳይ፣ ከአዉሮፓ እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመተባበር አይ ኤስ አይ ኤስን እና አልቃይዳን ለመዋጋት የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።
ማሊ እነዚህን ሄሊኮፕተሮች ከሩሲያ ፌዴሬሽን የገዛችዉ፣ “የሁል ጊዜም አጋሯ እና ፍሬያማ አጋርነት ካላት ወዳጅ ሃገር” ከሆነችዉ ሩሲያ መሆኑን ጠቅሰው፥ የጦር መሳሪያዎቹና ጥይቶቹን ደግሞ በስጦታ አበርክታልናለች ነው ያሉት የመከላከያ ሚኒስትሩ።
በአመለወርቅ ደምሰዉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
May be an image of one or more people and outdoors
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.