Fana: At a Speed of Life!

ማሊ ዴንማርክ ወታደሮቿን ከሀገሯ በፍጥነት እንድታስወጣ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ማሊ ከሰምምነት ውጭ በሀገሬ ሰፍረዋል ያለቻቸው የዴንማርክ ወታደሮች ከሀገር እንዲወጡ ጠየቀች።

የማሊ ወታደራዊ መንግስት ዴንማርክ ያለስምምነት በሀገሪቱ ያሰፈረችውን ከ100 የሚልቁ ወታደሮችን እንድታስወጣ ነው የጠየቀው።

የዴንማርክ ጦር በበኩሉ ወደ 90 የሚጠጉ ወታደሮች በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በማሊ የሚገኙትን የአውሮፓ የፀረ-ሽበር ዘመቻ አባላትን እንዲያግዙ ማሊ መግባታቸውን አስታውቋል።

ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ የተሰማሩት የዴንማርክ ወታደሮች በምስራቅ ማሊ በምትገኘው ሜናካ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፥ እስከ 2023 ድረስ በሀገሪቱ ቆይታ ያደርጋሉ ተብሎ ነበር፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.